በመጀመሪያ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ና ምስጋና ይሁን:: በዚህ ባለንበት ዘመን የሕይወት ምንጭ፥ የሁሉ ነገር መገኛና ባለሥልጣን የሆነው የእግዚአብሔርን ቃል በትህትና እና በቅን ልብ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ሆነው የመማር ልማድ ቸል የተባለ ይመስላል:: ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሆነው በዚህ በተማሪዎች ኅብረት (AAUPGSF) በተከታታይ ግሩም የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል እንድንማርእግዚአብሔር ዕድል ሰጠን::በነበረኝ ቆይታ እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዘመን ስንቅ የሚሆን፤ማንም ሊወስድብኝ የማይችለውን የቃሉን እውነት እንዳስታጠቀኝ እና ከኅብረቱ ጋር ግሩምና ድንቅ ጊዜ እንደ ነበረኝ ይሰማኛል::
ተመስገን ገልቹ፣
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪ