ቀዝቃዛ የስሜት ወላፈን፤ ፍርሃት፤ ባዶነትና በህይወት ሸለቆ ውስጥ ተሰፋ መቁረጥ፣ አሁን ያ ሁሉ አልፏል፡፡ ነገር ግን አንድን ነገር ያስታውሱኛል፣ “የእግዚአብሔር አደባባይ”፡፡ ፊቴ በርቶ፤ ልቤ ሞልቶ፤ ሀዘንና ጭንቀቴን ረስቼ፣ ፍጹም በሆነ ደስታ የምመለስበትን “የቅዱሳን ህብረትን” እግዚአብሔር ስለሰጠኝ፤ ስለጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት እጅግ በጣም ጌታን አመሰግናለሁ፡፡ በዚህ ስፍራ ጌታ አባብሎኛል፣ ግሩም በሆነ ምክሩ ከመታወቅ በላይ የሆነ ፍቅሩን አሣይቶኛል፡፡ ክብር ለሱ ይሁን! የቆሬ ልጆች በመዝ.84 ላይ “የሰራዊት አምላክ ሆይ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው! ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወዳለች፤ ትናፍቅማለች” ብለው እንደዘመሩ በቀረው የህይወት ዘመናችን ሁሉ የእግዚአብሔርን አደባባይ መናፈቅ ይብዛልን፡፡
አሜን!
ዓለማየሁ ባህሩ
ጅማ ዩንቨርሲቲ፣ የህክምና ትምህርት ተመራቂ ተማሪ