በአመታት ያልተለወጠው የዘመናት ጌታ ለኛ ደግሞ ይህንን ጊዜ ስላመጣልን ደስ ብሎኛል። ወደ ኃላ ዞር ብዬ ስመለከት ጐልተው የሚታዩ እንዳልክዳቸዉ ደምቀው የሚያበሩ የአምላክ የምህረት ቀናት ይታዩኛል። ደግሞም ጌታ በግቢ ስለሰጠኝ የተወደዱ ብሩካን ወንድም እና እህቶች አመስግኜ አልጠግብም፤ ዘማሪዉ እንዳለ “ባርካቸው” ብያለሁ።
ከፊት ባለን ኑሮ ደግሞ ትልቅ የባለ አደራነት ህይወት ይጠብቀናል፤ እናም ወዳጄ ሆይ ፥ ልበ ሰፊ ሁን፤ ዘመኑን ዋጅ፥ ንቃ፥ ወገብህን በቃሉ ቀበቶ እሰር፥ የወንጌሉን ጫማ ተጫማ። እንዲህ ልባርክህ “ሂድ ……… ተከናወን”::
ዶ/ር ሀይለእግዚአብሔር ይታገሱ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ተመራቂ