Skip to content

አዎ አሳክተነዋል! የመጀመሪያውን ወሳኝ የህይወታችን ምዕራፍ በአምላካችን ክንድ አጠናቀነዋል ፥እርሱም የመጀመሪያ ዲግሪ መያዛችን ነው።ውድ ተመራቂዎች እንኳን ለዚህ ቀን እግዚአብሔር አደረሳችሁ።ህይወት ረዥም ጉዞ ናት፥ በጉዞው ውስጥ የምናገኛቸው ስኬቶች እና መመረቃችን የራዕያችን ፍጻሜ ሳይሆን ለወደፊቱ ስኬታችን አና ግባችን መነሻ ነጥብ ናቸው። ይህ ምርቃት እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እና ተግተን ከሰራን አላማችንን ለማሳካት ምን ያህል አቅም አንዳለን ያሳየንበት አጋጣሚ ነው።በመጨረሻም በፌሎሺፑ እና በግቢ ውስጥ ስለነበረን የተወደደ ቆይታ አምላካችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፥እንዲሁም ውድ ተመራቂዎች በመጭው ህይወታችሁ በሁሉም የህይወት መስክ መልካም ፍሬያችሁ የበዛ እና እንደ ክዋክብት የምታበሩና የምትደምቁ ትሆኑ ዘንድ ከልብ እመኛለው።
አያና ስለሺ
Selam campus
Department: Textile and Apparel merchandising
Go to Top