ዉድ የ2009 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩኝ ላለፉት ጥቂት አመታት እግዚአብሔር በብዙ መንገድ እያስተማራችሁ፤ ከክብር ወደ ክብርም ሲለዉጣችሁ፤ ዓላማዉ በእናንተ ላይ ምን እንደሆነ እንድታወቁ ዘንድ እፈልጋለሁ፡፡ እርሱም በምትሠሩበት መሥሪያ ቤት ሁሉ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድታስከብሩ፣ በደረሳችሁበት ቦታ ሁሉ በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንድትሆኑ እና ስማችሁን ሳይሆን ስሙን እንድታስጠሩ ነዉ፡፡
እጣችሁ የእግዚአብሔር ሀሳብና ፈቃድ ባለበት ይዉደቅ! መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ፡፡
ክፍሌ ወልዴ
የኢቫሱ ደቡብ ክልል ቢሮ – የሙሉ ጊዜ አገልጋይ