እንኳን ደስ አላችሁ!!
ስለእናንተ ጌታን እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ውድ ተመራቂዎች፣ መመረቅ ከራስ አልፎ ለብዙዎች ጭምር ኅላፊነትንና ተጠያቂነትን ወደ ሕይወታችን ያመጣል:: ቃሉ “የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃል” እንደሚል፣ ከ2.8 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ በዓለም ዙርያ ገና ወንጌልን ሳይሰማ የእኛን መገለጥ ይጠብቃል። ወገኔ፣ በቀረልን ጥቂት ዕድሜ በየትኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ብንሆንም ለዚህ በሲዖል አፋፍ ላለ ሕዝብ እናስብ። የጌታን ክብር ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ለመግለጥ እንኑር። ወንጌልን በፀሎት ሃይል በመሄድ ፣ ሌሎችን በመላክ ፣ ስለ ጌታ የማያውቁ እንግዶችን በመቀበልና ሰዎችን ለወንጌል በማነሳሳት የእግዚአብሔርን ክብር መገለጫ እየሆንን፣ መንግሥቱን እስከ ዳግም ምፅአት ድረስ በማስፋት ፤ ታላቁን ተልዕኮ እየፈጸምን እስከ ምድር ዳርቻ እንሂድ።
ገዛኸኝ ሹመሮ
በደቡብ ኢቫሱ ቢሮ፣ የተማሪዎች አገልጋይ።