ትላንት ዛሬን አይደለም ዛሬም ደግሞ ነገን ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ሆኖም ግን ሰዎች ለእግዚአብሔር ሀሳብና እቅድ ከመኖር ይልቅ ለራሳቸው ሀሳብና ፍቃድ ሲኖሩ ይስተዋላል። መማራችንም ሆነ መስራታችን ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት። መፅሐፍ ቅዱስ በ2ኛ ቆሮ 5÷15 ላይ ሲናገር |“በህይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ ይላል።”
ስለዚህ ተመራቂ ተማሪዎች በቀረው የህይወት ዘመናችሁ ለእግዚአብሔር ሀሳብና ፍቃድ መኖር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
ወንደሰን ይበልጤ
የኢቫሱ ምዕራብ ክልል ቢሮ – የሙሉ ጊዜ አገልጋይ