በመጀመሪያ ለረዳን ላገዘን ባሳለፍናቸዉ ዓመታት ሁሉ በድካምም ሆነ በብርታት በፀጋዉና በምህረቱ ለደገፈን በህብረቶቻችን በነበረን ቆይታ ሁሉ በክብሩ እየተገለጠ ላስደነቀን ለምንወደዉ ጌታ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁንለት፡፡
በመቀጠል የዚህ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎችን ሁሉ እንኳን ደስ ያለን ማለት እወዳለው፡፡ በመጨረሻ ማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት የሀገራችን መንፈሳዊ እና ምድራዊ ተኃድሶ የሚመጣዉ በእኛ እንደሆነ አምናለሁ፤ ስለሆነም ሁላችንም በተማርንበት የሞያ ዘርፍ በማቴዎስ 5፡13-14 ላይ እንደተጠቀሰዉ የምድር ጨዉና የዓለም ብርሃን በመሆን ለእግዚአብሔር ክብር፤ እርሱን በመፍራት፤ በጽድቅ በገባንበት ሥፍራ ሁሉ ክርስቶስን ማሳየት እንዲሆንልን ያስፈልጋል፤ እንዲሆንም ከልቤ ዘወትር እፀልያለሁ፤ እመኛለሁ፤ እናፍቃለሁ ሁላችንንም ጌታ ይርዳን፡፡ በኢቫሱ የሚያገለግሉትን፤ እንዲሁም የሚቀሩ ተማሪዎችን ሁሉ አምላኬ እግዚአብሔር ይባርካችሁ በጣም እወዳችኋለሁ፡፡
ግሩም አለማየሁ
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ በሶሻል ወርክ ተመራቂ ተማሪ