በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ) አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የክርስቶስ ልኅቀት ትምህርታዊ ጉባኤ ( Supremacy of Christ Teaching Conference) ፣ ዛሬ በደቡብ ኢቫሱ አዘጋጅነት፣ በሀዋሳ ይጀመራል፡፡ ጉባኤው ከመካከለኛው ኢቫሱ ክልል ላለፉት አራት ዓመታት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመትም ጉባኤው ከ የካቲት 23-25 ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡ በዝግጅቱም ከሁለት ሺ አምስት መቶ በላይ ተዳሚዎች ተካፍይ ሆነዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉባኤው፣ በሌሎች የኢቫሱ ክልሎችም መካሄዱ ጠቃሚነቱ የጎላ መኾኑ ታሞኖበት በ2009 ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ክልል፣ በድሬዳዋ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ዓመትም ቀጥሎ ፣ ጉባኤው፣ በደቡብ ኢቫሱ ክልል ሀዋሳ ከተማ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች፣
እንዲሁም የቤተክርስቲያን ወጣቶችና ምሩቃን ይታደማሉ፡፡
ጉባኤው የሚካሄደው በሀዋሳ ሞቢል ሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ሲሆን፣ የፕሮግራሙ መርሐ ግብር
ዐርብ፡ ከ10፡30 – 2፡30፣ ቅዳሜ ከ3፡00- 6፡00 እና ከ 10፡00-2፡30 እንዲሁም እሁድ ከ 4፡00 ጀምሮ፣ በዛው እለት ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
በአካባቢው የምትገኙ ቅዱሳን በዝግጅቱ ተካፋይ በመሆን የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል፡፡