በዚህ መንገድ የለም

ገበያን ሳስበው ገና ከቤቴ ሳልወጣ ድካም ይሰማኛል፣ ግን ደግሞ የግድ መርካቶ መሄድ ነበረብኝ፣ ጫማ ልገዛ፤ ደግሞ እግሬ ትልቅ ነው (አርባ ቁጥር)፣ ጫማ ሻጮች ሁሌም ግርም ይላቸዋል፡- የቁመቴ ማነስና የእግሬ መተለቅ፣ እኛ አገር ደግሞ ትልቅ ቁጥር ጫማ እንደ ልብ አይገኝም፤ እህቴ “ጫማው ነው የሚመርጥሽ” እያለች ትቀልድብኝ ነበር፡፡ ወሩ ጥቅምት እንደነበር ትዝ ይለኛል ዓመተ ምህረቱ ደግሞ 2002፤…