ለመስማት መቅረብ

ለመስማት መቅረብ…   እግዚአብሔር ተናጋሪ አምላክ ነው፡፡ ሐሳብ ስላለው ይናገራል፤ ዓላማ ስላለው ይናገራል፤ ግብ ተኮር ስለሆነ ይናገራል፤ አፍቃሪም ስለሆነ ይናገራል፡፡ ከመጀመሪያው አንስቶ ሲናገር ነበር፡፡ ፍጥረትን እንኳ ወደ መኖር ያመጣው አናግሮ ነው፡- “ይሁን” እያለ፡፡ ሲፈጥር እንደ ተናገረ፤ ከፈጠረም በኋላ ተናግሯል፤ ባርኳል፡- “ብዙ ተባዙ…ግዟቸው” (ዘፍ 1፥28) ብሎ፤ መመሪያ ሰጥቷል፡- “አትብላ…ትሞታለህ” ብሎ (ዘፍ 2፥17)፡፡ ሰው ሲወድቅም መናገር ቀጠለ፣…