የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት መሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር (ኢቫሱ)፣ የሚዘጋጀው ዓመታዊው የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች፣ የመሪዎች ጉባኤ ደብረዘይት በሚገኘው የመሠረተ ክርስቶስ ኮሌጅ ለስድስት ቀናት ሲካሄድ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ቅዳሜ ማታ (ነሐሴ 13/2009 ዓ.ም) ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ የጉባኤው መሪ ሐሳብ፣ በካምፓስ ውስጥ << ለኢየሱስ መኖር፤የኢየሱስ ምስክር መሆን>> የሚል ነበር፡፡ በስድስቱ ቀናቶች በዚሁ መሪ ሐሳብ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ትምህርቶችና…