ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ (219) ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጨመሩ

“ መከሩስ ብዙ ነው፥…..” ሉቃስ 10፡2 የቀደሙ የዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች፣ ለተመደቡበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን የክርስቶስ መልእክተኛ አድርገው ይቆጥሩ እንደነበር የጽሑፍ መረጃዎች ይናገራሉ፡፡ ለህትመት እየተዘጋጀ ያለው የኢቫሱ የታሪክ ሰነድም ይኼን እውነት ከባለታሪኮቹ አንደበት ቀድቶ እንዲህ ያስነብበዋል፡- “እኛ የካምፓስ ወንጌላውያን ነን፡፡ . . . እኛ እያለን እግዚአብሔር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሌላ የወንጌል መልዕክተኛ አይልክም፤ ወንጌልን ለአቻዎቻችን…