የኢቫሱ- ቤተክርስቲያን እና አጋር አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ)፣ ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አጋር አካላት ያዘጋጀው የአንድ (1) ቀን   የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ባለፈው የካቲት 15 /2010 ዓ.ም በሳሮ-ማሪያ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ኢቫሱ፣ የቤተክርስቲያን አጋዥ ተቋም ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በከፍተኛ ተቋማት የሚገኙትን የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን እያገለገለ የሚገኘው፣ ይኸው ተቋም(ኢቫሱ)፣ ከተመሰረተ  ሃምሳ ሦስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ወንጌላውያን ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተገቢውን…