የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር(ኢቫሱ)፣ ከተመሰረተ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ከምስረታው (ከ1957 ዓ.ም) ጀምሮ  ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ማኅበሩ ፣ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የእግዚአብሔር መንግስት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ውስጥ እንዲሰፋ እየሰራ ይገኛል፡፡ በእስከአሁኑ አገልግሎቱም፣ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የቤተክርስቲያን  እና ሀገር መሪዎችን፣ አገልጋዮችን፣ በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር የታነፁ ባለሙያዎችን ማፍራት ችሏል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በከፍተኛ…