“ስማርት” የንዑስ ቡድን

በኮቪድ19  ምክንያት የተቋረጡትን በኢቫሱ ሕብረቶች ሲደረጉ የነበሩትን የንዑስ ቡድኖች እንዴት ማስቀጠል ይቻላል? “ስማርት” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል፤ ጉብዝናን፣ ፍጥነትንና ቅልጥፍናን አመልካች ሲሆን በ21ኛው ክፍለዘመን በተጨማሪነት ኢንተርኔትን ለሚጠቀሙ ቁሶችም በገላጭነት እንጠቀምበታለን፡፡ በሚከተለው አጭር ጽሑፍ በየካምፓሶቹ በኢቫሱ ሕብረቶች ሲደረጉ የነበሩትን የንዑስ ቡድኖችን በኮቪድ19 ስለተቋረጡ ዘመኑ ባጎናፀፈን  የመገናኛ ቴክኖሎጂ ተጠቅመን እንዴት ማስቀጠል እንደሚቻል እንመክራለን፡፡  የኢቫሱ ዋና ዓላማ “ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት” ነዉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸዉ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታቸዉ እና አዳኛቸዉ እንዲከተሉ እንዲሁም ከዚህ ምልልስ የወጣ የምስክርነት ሕይወት (የቃል እና የኑሮ) እንዲኖራቸዉ በትጋት ይሰራል፡፡ ይህንንም ዓላማ ከግብ ለማድረስ እንደ ዋና የአገልግሎት ስልት የሚጠቀመው የንዑስ ቡድን አገልግሎትን…