የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር(ኢቫሱ)፣ ከተመሰረተ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ከምስረታው (ከ1957 ዓ.ም) ጀምሮ  ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ማኅበሩ ፣ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የእግዚአብሔር መንግስት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ውስጥ እንዲሰፋ እየሰራ ይገኛል፡፡ በእስከአሁኑ አገልግሎቱም፣ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የቤተክርስቲያን  እና ሀገር መሪዎችን፣ አገልጋዮችን፣ በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር የታነፁ ባለሙያዎችን ማፍራት ችሏል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በከፍተኛ…

የ2010 ዓ.ም የክርስቶስ ልዕልና ጉባኤ

በኢቫሱ የመካከለኛው ክልል ቢሮ በየዓመቱ የሚካሔደው የኢየሱስ ክርስቶስ ልዕልና ትምህርታዊ ጉባኤ፣ በተማሪዎች አልፎም በአዲስ አበባ እና አካባቢው ባሉ ምሩቃን፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና የቤተክርስቲያን ወጣቶች ዘንድ ተጠባቂ እየሆነ የመጣ ፕሮግራም ነው፡፡ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የተደረገው የኢየሱስ ክርስቶስ ልዕልና ኮንፍራንስ በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን፣ ከየካቲት 23 እስከ 25 2010 ዓ.ም ድረስ፣ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡ ለመጀመርያ…

የኢቫሱ- ቤተክርስቲያን እና አጋር አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ)፣ ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አጋር አካላት ያዘጋጀው የአንድ (1) ቀን   የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ባለፈው የካቲት 15 /2010 ዓ.ም በሳሮ-ማሪያ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ኢቫሱ፣ የቤተክርስቲያን አጋዥ ተቋም ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በከፍተኛ ተቋማት የሚገኙትን የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን እያገለገለ የሚገኘው፣ ይኸው ተቋም(ኢቫሱ)፣ ከተመሰረተ  ሃምሳ ሦስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ወንጌላውያን ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተገቢውን…

የክርስቶስ ልኅቀት ትምህርታዊ ጉባኤ፣ በደቡብ ኢቫሱ

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ) አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የክርስቶስ ልኅቀት ትምህርታዊ ጉባኤ ( Supremacy of Christ Teaching Conference) ፣ ዛሬ በደቡብ ኢቫሱ አዘጋጅነት፣ በሀዋሳ ይጀመራል፡፡ ጉባኤው ከመካከለኛው ኢቫሱ ክልል ላለፉት አራት ዓመታት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመትም ጉባኤው ከ የካቲት 23-25 ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡ በዝግጅቱም ከሁለት ሺ አምስት መቶ በላይ ተዳሚዎች…

92 በታኅሳስ እና 352 ተማሪዎች ባለፉት ሶሰት ወራት ጌታን ተቀበሉ

 “. . . አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ በታላቅም ድምፅ እየጮሁ። በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ።” ራእይ 7:9 በታኅሳስ ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀያ ሁለት ካምፓሶች ውስጥ ዘጠና ሁለት ተማሪዎች ጌታን ተቀብለዋል፡፡ እነዚህ…

ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ (219) ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጨመሩ

“ መከሩስ ብዙ ነው፥…..” ሉቃስ 10፡2 የቀደሙ የዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች፣ ለተመደቡበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን የክርስቶስ መልእክተኛ አድርገው ይቆጥሩ እንደነበር የጽሑፍ መረጃዎች ይናገራሉ፡፡ ለህትመት እየተዘጋጀ ያለው የኢቫሱ የታሪክ ሰነድም ይኼን እውነት ከባለታሪኮቹ አንደበት ቀድቶ እንዲህ ያስነብበዋል፡- “እኛ የካምፓስ ወንጌላውያን ነን፡፡ . . . እኛ እያለን እግዚአብሔር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሌላ የወንጌል መልዕክተኛ አይልክም፤ ወንጌልን ለአቻዎቻችን…

አርባ አንድ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጨመሩ

“መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዴህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።” ሉቃስ 10፡2 በጥቅምት ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ በአስራ አምስት ካምፓሶች ውስጥ አርባ አንድ ሰዎች ጌታን ተቀብለዋል፡፡ እነዚህ ወንድሞች እና እህቶች በዋናነት ወደ ጌታ የመጡት በተማሪዎችና በክርስቲያን የተማሪ ህብረቶች ውስጥ በሚካሔድ የንዑስ ቡድኖች እና በመደበኛ የህብረቱ አገልግሎት አማካኝነት ነው፡፡ ተማሪዎችን ደቀመዝሙር ለማድረግ…

ዓመታዊ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት መሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

  በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር ( ኢቫሱ)፣ የሚዘጋጀው ዓመታዊው የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች፣ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል፡፡  ብሔራዊ ጉባኤው፣ ከ አንድ መቶ ሃምሣ ስምንት (158) የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ የክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች የሚወከሉ የተማሪ መሪዎች የሚሣተፉበት ሲሆን፣ የተሣታፊዎቹ ቁጥርም አምስት መቶ (500) እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ዓመት፣ የጉባኤው መሪ ሐሳብ ፣ በካምፓስ ውስጥ…