Responding to COVID-19
ለኮቪድ-19 ምላሽ መስጠት
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እየተከሰተ ያለው በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ ነው:: ይህ በሽታ በእኛም አገር ከፍተኛ ስጋት ሆኗል:: በዚህ ጊዜ ዩኒቨርቲዎችና ኮሌጆች በመዘጋታቸው ምክንያት የኢቫሱም አገልግሎት ተፅዕኖ ውስጥ ይገኛል::
ይሁንና መልካሙ ዜናችን: ስንሰጠው የነበረው አገልግሎታችን የስልት ለውጥ ያደርግ ይሆናል እንጂ በፍፁም አይቆምም:: ምክንያቱም “…ጊዜው ቢመችም ባይመችም…”(2ኛ ጢሞ 4:2) አገልግሎታችን እንዲቀጥል የጌታ ቃል ያበረታታናል:: ይልቁንም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዓላማችን የሆነውን “የእግዚያብሔርን መንግስት ማስፋትን” በምንም ሳንደናቀፍ ለመቀጠል በእግዚያብሔር ተደግፈን ለጊዜው የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት የኢቫሱ ቦርድ: ተማሪዎች: ምሩቃንና አገልጋዮች እየሰራን እንገኛለን::
በዚህ ድኽረ ገፅም ኢቫሱ ለዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምላሽ የምንሰጥባቸው የፀሎት ጥሪዎች: ለመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት የሚጠቅሙ ግብዓቶች (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችና መጣጥፎች) እና ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ::
The coronavirus pandemic has created a devastating threat and tragic situation globally. It has created huge concerns within our country. Because of the shutdown of universities and colleges in Ethiopia, the worldwide crisis has also impacted EvaSUE’s ministry.
The good news, however, is that we who are EvaSUE will not stop what God has called us to do. We will make some strategic changes in light of the current situation and continue serving students wherever they are. Our motivation comes from the word of God which encourages us to continue our ministry “in season and out of season” (2 Timothy 4:2). All of us at EvaSUE—the board, students, graduates, and staff—are relying on God to help us as we give a timely response to this pandemic and strive to fulfill our mission, which continues to be, “advancing the Kingdom of God”.
On this page, you will find useful information regarding the current situation we are in, along with prayer requests and resources (Bible studies) that will enable you to continue growing spiritually.

“ሰላሜን እሰጣችኋለሁ” የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ኢየሱስ በሕማማቱ ሳምንት የተናገራቸው የማፅናኛ ንግግሮች ላይ የተመሰረተ