Skip to content
የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ኢቫሱን ተቀላቀሉ
You are here:
- Home
- News
- የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ኢቫሱን ተቀላቀሉ
ባለፉት ሶስት አመታት፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር(ኢቫሱ) ተግቶ እየሰራ እንዲሁም እመርታ እያሳየ ካለባቸው የትኩርት አቅጣጫዎች መሀከል የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን በማብዛት፣ በእያንዳንዱ ካምፓስ የወንጌላውያን ተማሪዎችን ማገልገል አንዱ ነው፡፡ በዚሁም መሰረት በ2010 ዓ.ም አስራ ስድስት የካምፓስ አገልጋዮች የኢቫሱን የተማሪዎች አገልግሎት ተቀላቅለዋል፡፡
እነዚህ አገልጋዮች በሚኖራቸው የአንድ አመት ቆይታ በህብረቶች ውስጥ በዋናነት ሚናቸው ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡11-12 ለጢሞቴዎስ በመከረው መሰረት፣ መንገድ ማሳየት፣ ማስተማር እና አርአያ መሆን ነው፡፡
እነዚህ አገልጋዮች በሚኖራቸው የአንድ አመት ቆይታ በህብረቶች ውስጥ በዋናነት ሚናቸው ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡11-12 ለጢሞቴዎስ በመከረው መሰረት፣ መንገድ ማሳየት፣ ማስተማር እና አርአያ መሆን ነው፡፡ አገልጋዮቹ በካምፓስ በነበራቸው ቆይታ በወንጌላውያን ህብረቶች መሪነት ያለፉ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቅርብ አመት ምሩቃን ናቸው፡፡ ይህም በሚኖራቸው የቀጣይ አመት አገልግሎት የሚያገለግሉትን ተማሪ ባህሪ እና ከባቢ ለመረዳት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ እንደሚሆንላቸው ይጠበቃል፡፡
እነዚህ የኢቫሱን አገልግሎት በሙሉ ጊዜ ለመቀላቀል የወሰኑ ወንድሞች እና አህቶች የካምፓስ ሚሽን ሞብላይዜሽን ፕሮጀክት(ስልጠናን የተከታተሉ) ውስጥ ያለፉ ናቸው፡፡ የካምፓስ ሚሽን ሞብላይዜሽን በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር(ኢቫሱ) እና በሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢቫንጀሊካል ሚሽን ኢንጌጀርስ ትብብር የሚተገበር የአምስት አመት ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ እቅዱ ምሩቃንን በየአመቱ በማሰልጠን አስር የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን በየአመቱ በማሰማራት ወንጌላውያን ተማሪዎችን ለእግዚአብሔር ተልእኮ ማስተማበር ሲሆን፤ በረጅም
ጊዜ ዕቅዱ ደግሞ የወንጌላውያን ተማሪዎች እንቅስቃሴ ተልኮዋዊ ሆኖ ማየት አላማው አድርጎ እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህም ፕሮጅከት ባለፉት አራት አመታት ትልቅ እመርታ ማሳየት የቻለ ፕሮጀክት ነው፡፡ ለዚህም ስኬት ሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢቫንጀሊካል ሚሽን ኢንጌጀርስን ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጎዋል፤ ስለሆነም ኢቫሱ አጋሩ የሆነውን ይህን የሚሽን ኤጀንሲ እና አገልጋዮቹን ለማመስገን ይወዳል፡፡
Go to Top