
እንኳን ወደ ኢቫሱ የብሔራዊ ጉባኤዎች መመዝገቢያ ቅፅ በደህና መጡ!
ስለፕሮግራሞቹ
የኢቫሱ ዋና አላማ ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ነዉ። ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ልዩ ልዩ ስልቶችን የሚጠቀም ሲሆን አገልጋይ መሪዎችን ማብቃት ከስራዎቹ አንዱ ነው። ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተማሪ መሪዎችን ለማስታጠቅ እና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ሲሆን ብሔራዊ የሚሽን ጉባኤ ደግሞ በወንጌል ማስተማበር እና በማህበራዊ አገልግሎት ዙሪያ የሚያገለግሉ የተማሪ መሪዎችን ለማስታጠቅ እና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ነው።
የምዝገባ ዝርዝር መረጃ
ብሔራዊ የሚሽን ጉባኤ
(National Mission Summit)
- ቀን፡ ሐምሌ 1 - 6/ 2016 (July 8 – 13/ 2024) ተማሪዎች የሚገቡት ሰኞ ሐምሌ 1 ሲሆን፤ ቅዳሜ ሐምሌ 6 የሚወጡበት ቀን ይሆናል፡፡
- ቦታ፡- ደብረዘይት መሰረተ ክርስቶስ ኮሌጅ
- የተሳታፊ ተማሪዎች ኮታ: ከየግቢዉ ከ3-5 Evangelism Mobilizers እና 2 Social Affairs Team Mobilizers
- የመመዝገቢያ ክፍያ: ለመንግስት ዩኒቨርስቲዎች - 900 ብር ፤ ለግል ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች - 700ብር
- የተሳታፊ ተማሪዎች ምዝገባ ማብቂያ ቀን፡ ሰኔ 7 /2016 (June 14/2024)
ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ
(National Leadership Summit)
- ቀን፡ ነሐሴ 13 – 18/ 2016 (August 19 -24/ 2024) ተማሪዎች የሚገቡት ሰኞ ነሐሴ 13 ሲሆን፤ ቅዳሜ ነሐሴ 18 የሚወጡበት ቀን ይሆናል፡፡
- ቦታ፡- ደብረዘይት መሰረተ ክርስቶስ ኮሌጅ
- የተሳታፊ ተማሪዎች ኮታ፡ የየግቢዉ ዋና መሪዎች በሙሉ (ከ7-9 ተማሪዎች)
- የመመዝገቢያ ክፍያ: ለመንግስት ዩኒቨርስቲዎች - 900 ብር ፤ ለግል ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች - 700ብር
- የተሳታፊ ተማሪዎች ስም እና ክፍያ ምዝገባ ማብቂያ ቀን፡ ሐምሌ 12 /2016 (July 19 /2024)
ማሳሰቢያ
- ወደ ፕሮግራሙ ሲመጡ በኢሜል የተላከውን ደረሰኝ ይዘው ይምጡ
- ምዝገባው በአንድ ተወካይ ሰው በኩል ብቻ የሚፈፀም ይሆናል
- ክፍያ በሙሉ በቴሌ ብር ይከናወናል
- ተምዝግቦ የሚቀር ሰው መተካት የሚቻለው በተመሳሳይ ፆታ ከሆነ ብቻ ነው
- ክፍያ ካልተጠናቀቀ በቀር ምዝገባው ውድቅ ይሆናል
- የክፍያ ደረሰኝ ፎርም ላይ ባስገቡት የኢሜል አድራሻ የሚላክ ይሆናል
- የኮሌጅ ስም ዝርዝር ውስጥ ከሌለ “other” የሚለውን መርጠው ይፃፉ። የኮሌጅ ስም ሲፅፉ ግን ሙሉ ስም ከነቦታው መጻፍ እንዳይረሱ