የ2010 ዓ.ም የክርስቶስ ልዕልና ጉባኤ

በኢቫሱ የመካከለኛው ክልል ቢሮ በየዓመቱ የሚካሔደው የኢየሱስ ክርስቶስ ልዕልና ትምህርታዊ ጉባኤ፣ በተማሪዎች አልፎም በአዲስ አበባ እና አካባቢው ባሉ ምሩቃን፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና የቤተክርስቲያን ወጣቶች ዘንድ ተጠባቂ እየሆነ የመጣ ፕሮግራም ነው፡፡ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የተደረገው የኢየሱስ ክርስቶስ ልዕልና ኮንፍራንስ በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን፣ ከየካቲት 23 እስከ 25 2010 ዓ.ም ድረስ፣ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡ ለመጀመርያ…